Category grid
የኤሌክትሪክ ክፍያዎ እንዴት ይሰላል? ማወቅ ያለብዎት ዝርዝር መረጃ
በየወሩ የሚደርሰዎ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ሂሳብ እንዴት እንደሚሰላ እና ለምን ምን ጉዳዮች እንደሚከፍሉ ጠይቀው ያውቃሉ? ብዙ ደንበኞች ከኃይል ፍጆታው በተጨማሪ የሚጨመሩ ክፍያዎች ግልጽ ስላልሆኑላቸው ቅሬታ ሲያቀርቡ ይስተዋላል።
የጂሜል ተጠቃሚዎች የቆዩ መጠሪያ ስሞቻቸውን ሊቀይሩ ነው
የቴክኖሎጂው ግዙፍ ኩባንያ ጎግል፣ የጂሜል ተጠቃሚዎች ከዓመታት በፊት አካውንት ሲከፍቱ የመረጧቸውን እና በአሁኑ ወቅት የማይመቿቸውን የተጠቃሚ ስሞች በቀላሉ መቀየር የሚችሉበትን አዲስ አማራጭ ሊያስተዋውቅ መሆኑ ተጠቆመ።
ግብጽ፣ ሶማልያ፣ ቱርክ እና ጅቡቲ የእስራኤልን ውሳኔ ተቃወሙ።
እስራኤል ከሰአታት በፊት ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅናን መስጠቷን ተከትሎ አራቱ አገራት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ከደቂቃዎች በፊትም የጋራ የስልክ ውይይት አድርገዋል።
እስራኤል ለሶማሊላንድ የሃገርነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሃገር ሆነች።
ላለፉት 30 አመታት የሃገርነት እውቅና ለማግኘት ጥረት ላይ የነበረችው የነበረችው ሶማሊላንድ በመጨረሻም ሙከራዋ ተሳክቶ ከእስራኤል የሃገርነት እውቅና አግኝታለች።
ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አከናወነ፤ የዶላር ዋጋ መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ታኅሣሥ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ባከናወነው የዓመት መጨረሻ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ የዶላር ዋጋ ካለፉት ሳምንታት አንጻር መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱን አስታወቀ።
በደሴ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ መደርመስ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ
በአማራ ክልል ደሴ ከተማ አስተዳደር "መንበረፀሐይ" ተብሎ በሚጠራው የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ትናንት በደረሰ የመንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመር ጥናት ማጠናቀቋን ይፋ አደረገች
በርበራን፣ ሞምባሳን፣ ጂቡቲና ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ ሁሉንም ወደቦች በባቡር መስመር ለማገናኘት ያቀደውን ፕሮጀከት ጥናት በኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ባለሙያዎች መሠራቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዓለም አቀፍ የገበያ መድረክ የአንድ ወቄት የወርቅ ዋጋ 4,561.4 ዶላር በመድረስ የምንግዜም ከፍተኛውን የታሪክ የዋጋ ደረጃ ዛሬ ዓርብ ዕለት አስመዘገበ
በዓለም አቀፍ የብረታ ብረት መገበያያ ገበያ የወርቅ ዋጋ ታይቶ የማይታወቅ ጭማሪ በማሳየት አዲስ የታሪክ ማይል ድንጋይ አስመዘገበ። በኒውዮርክ የንግድ ማዕከል የካቲት ወር ላይ ለሚረከቡ የወርቅ ውሎች (Gold Futures) የቀረበው ዋጋ በአንድ ወቄት (Ounce) 4,561.4 ዶላር በመድረስ የምንግዜም ከፍተኛው ሆኖ ዓርብ ዕለት ተመዝግቧል።
ቻይና የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ላይ የ13 በመቶ ታክስ በመጣል የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲዋን በከፍተኛ ሁኔታ ቀየረች
ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል የቤተሰብ ምጣኔን ለማበረታታት የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን ከቀረጥ ነፃ ስታቀርብ የቆየችው ቻይና፣ ከመጪው ጥር 2026 ጀምሮ ኮንዶሞችን ጨምሮ በሌሎች የወሊድ መቆጣጠሪያ ምርቶች ላይ የ13 በመቶ ታክስ ለመጣል መወሰኗን አስታወቀች።
የቀድሞው ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል የ7 ዓመት ከ2 ወር እስር ተፈረደባቸው
የቀድሞ የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ) አባል የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት በዛሬው ዕለት የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው።
" ዛሬ እና ነገ ወደ ደሴ የሚያደረገውን በረራ ለማቋረጥ ተገድጃለሁ " የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በደሴ እና አካበቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት በዛሬው እና በነገው ዕለት ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ መገደዱን አሳውቋል። አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚደርሰው መረጃ መሰረት የአየር ፀባዩ እንደተስተካከለ በረራዎቹ ወደመደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። በአገልግሎቱ መቋረጥ ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታም ጠይቋል።
ቻይና የወሊድ የህክምና ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ
የቻይና መንግስት በሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ የመጣውን የህዝብ ቁጥር ለመታደግ እና የውልደት ምጣኔን ለማሳደግ በማለም ከመጪው 2026 የፈረንጆቹ ዓመት ጀምሮ ማንኛውም ከወሊድ ጋር የተያያዘ የህክምና ወጪ በመንግስት እንዲሸፈን መወሰኑን አስታውቋል።