Category grid

ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመር ጥናት ማጠናቀቋን ይፋ አደረገች

ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመር ጥናት ማጠናቀቋን ይፋ አደረገች

በርበራን፣ ሞምባሳን፣ ጂቡቲና ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ ሁሉንም ወደቦች በባቡር መስመር ለማገናኘት ያቀደውን ፕሮጀከት ጥናት በኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ባለሙያዎች መሠራቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቻይና የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ላይ የ13 በመቶ ታክስ በመጣል የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲዋን በከፍተኛ ሁኔታ ቀየረች

ቻይና የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ላይ የ13 በመቶ ታክስ በመጣል የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲዋን በከፍተኛ ሁኔታ ቀየረች

ለሦስት አስርት ዓመታት ያህል የቤተሰብ ምጣኔን ለማበረታታት የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን ከቀረጥ ነፃ ስታቀርብ የቆየችው ቻይና፣ ከመጪው ጥር 2026 ጀምሮ ኮንዶሞችን ጨምሮ በሌሎች የወሊድ መቆጣጠሪያ ምርቶች ላይ የ13 በመቶ ታክስ ለመጣል መወሰኗን አስታወቀች።

" ዛሬ እና ነገ ወደ ደሴ የሚያደረገውን በረራ ለማቋረጥ ተገድጃለሁ " የኢትዮጵያ አየር መንገድ

" ዛሬ እና ነገ ወደ ደሴ የሚያደረገውን በረራ ለማቋረጥ ተገድጃለሁ " የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በደሴ እና አካበቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት በዛሬው እና በነገው ዕለት ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ መገደዱን አሳውቋል። አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚደርሰው መረጃ መሰረት የአየር ፀባዩ እንደተስተካከለ በረራዎቹ ወደመደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። በአገልግሎቱ መቋረጥ ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታም ጠይቋል።

ቻይና የወሊድ የህክምና ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ

ቻይና የወሊድ የህክምና ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ

የቻይና መንግስት በሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ የመጣውን የህዝብ ቁጥር ለመታደግ እና የውልደት ምጣኔን ለማሳደግ በማለም ከመጪው 2026 የፈረንጆቹ ዓመት ጀምሮ ማንኛውም ከወሊድ ጋር የተያያዘ የህክምና ወጪ በመንግስት እንዲሸፈን መወሰኑን አስታውቋል።